የአፍሪካ የደረጃዎች ድርጅት ፕሬዝዳንት እና የጋና ደረጃዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አሌክስ ዶዶ ኢተምድን ጎበኙ::

የአፍሪካ የደረጃዎች ድርጅት ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አሌክስ ዶዶ የኢተምድን የፍተሻ ላብራቶሪዎች ጎበኙ፡፡ ፕሬዝዳንቱ በጥራት መንደር ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት 9 የፍተሻ ላቦራቶሮች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አቤል አንበርብር ድርጅቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡