
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ሠራተኞች እና ሥራ አመራሮች 129ኛውን የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም አከበሩ፡፡ በዓሉን የተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል መሆኑንና መላው ሠራተኛ በተሰማራበት የሥራ መስክ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንደተቋም ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ከብልሹ አሰራር የፀዳ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ድርጅቱ የተጣለበትን የሀገር ኢኮኖሚ የመደገፍ ተልዕኮ በብቃት እንዲወጣ ትጋትና ጥንካሬን በመላበስ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት በመሥራት አባቶቻችን ሀገርን እንደጠበቁ እኛም የሀገር ሠላምን ልንጠብቅ ለልጆቻችን እዳን ሳይሆን ምንዳን ልናወርስ ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የዓድዋ የድል በዓል በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የካቲት 23 ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።