
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የልማት ድርጅቶች ቢሮ የኦ-ፕሮዲውስ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሥር የሚገኙ 6 አምራች ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች በዘመናዊ የፍተሻ ቴክኖሎጂዎችና ባለሙያዎች የተደራጁትን የጥራት መንደር ተቋማት ጎበኙ፡፡
በጉብኝታቸው ጥራትን የሚያረጋግጡ በዘመናዊ የፍተሻ መሳሪያዎች የተደራጀውን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የፍተሻ ላብራቶሮች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ በተለይም በጥራት መንደሩ የሚገኙ ተቋማት በአምራች ኢንዱስትሪው የሚመረቱ ምርቶችን ጥራት ከማረጋገጥ አንፃር ኢተምድ እየሰጣቸው ስለሚገኘው አገልግሎቶች ገለፃና ማብራሪያ አድርገውላቸዋል፡፡ በተጨማሪም በኢንቨስትመንት ግሩፑ ስር የሚገኙት እነዚህ ድርጅቶች የሚያመርቷቸው ምርቶች የጥራት ደረጃን የጠበቁ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በተስማሚነት ምዘና ሂደት የሚያልፋበትን አግባብ በተመለከተ በቀጣይ በጋራ በሚሰሩ ሥራዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
Related Posts
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡