
ለጨጨሆ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ የምግብ ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት( ISO 22000:2018 Food safety Management system) እና winner pipes የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015 Quality Management system) ሰርቲፊኬት ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂኔር መአዛ አበራ ተረክቧል።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂኔር መአዛ አበራ ዓለም አቀፍ የስራ አመራር ስርዓት ሰርቲፊኬት ማግኘታቹ ለሚትሰጡት አገልግሎት ሆነ ለሚታመርቱት ምርት በሀገር ውስጥና በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲትሆኑ አስቻይ መሆኑን በርክክቡ ወቅት አብራርቷል አክለውም የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ሰርቲፋይድ ለሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ሰፊ ገለፃ ያደረጉላቸው ሲሆን በመጨረሻም የእንኳን ደስአላችሁ መልእክትም አስተላልፏል።
የሁለቱም ሰርቲፋይድ የሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች በበኩላቸው ለጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ዓለምአቀፍ ሥራ አመራር ሥርዓት አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተን ሰርቲፋይድ በመሆናችን በዓለምአቀፍ ደረጃ ተመራጭ እንድንሆን ወሳኝ ሚና ስለሚጫወት እና ድርጅቱም ላደረገው ሙያዊ የአዲት ስራ እጅግ ደስተኞች መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን አክለውም ሰርተፍኬቱ ለቀጣይ ስኬት አነሳሽ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
Related Posts
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡