
ማማ ወተት በሚለው የብራንድ ስሙ የሚታወቀው ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ የምግብ ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት( ISO 22000:2018 Food safety Management system) እና የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015 Quality Management system) ሰርተፊኬት ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ተረክቧል።
የኢትዮጵያ ተስማሚነት እና ምዘና ድርጅት የኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አቤል አንበርብር በጥራት ለሚያመርቱ አምራቾች እውቅና መስጠት በሀገር ውስጥና በዓለምአቀፍ ደረጃ የገበያ ተወዳዳሪነትን ያጠናክራል ሲሉ በርክክቡ ወቅት ተናግረዋል።
የሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሳራ ሀሰን በበኩላቸው ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ለምግብ ደህንነት እና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ዓለምአቀፍ የምግብ ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 22000:2018 Food safety Management system) እና ዓለምአቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015 Quality Management system) ሰርቲፋይድ መሆኑን የገለፁ ሲሆን አክለውም ሰርተፍኬቱ ለቀጣይ ስኬት አነሳሽ እንደሆነ ተናግረዋል::
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።