የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚ/ር የክልልና የከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የክልልና የከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ “በጥራት ወደ ተሳለጠ የንግድ ሥርዓት” በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 7-8/2017 ዓ/ም በማእከላዊ አትዮጵያ ቢሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቡታጅራ ከተማ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ጉባኤው የከፈቱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቢሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር እንደሻው ጣሰው ክልሉ ነሀሴ 13 /2013ዓ.ም የተመሰረተ መሆኑን አውስተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት በማስተላለፍ ፕሮግራሙን ስኬታማ እና ውጤታማ ፕሮግራም እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ከፍቶታል።
በጉባኤው መክፈቻ ፕሮግራም ላይ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ደ/ር ካሳሁን ጎፌ እንደ ሃገር ሰፊና ዘመናዊ የጥራት መንደር ተገንብቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሰረተልማት ገንብተን አገልግሎት እየሰጠን መሆናችን እና በእነዚህ መሰረተ ልማት ተጠቅመን በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ ምርቶች ተመራጭና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን ከውጭ ሃገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ምርቶችም ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ እና የህብረተሰባችንን ጤንነትና ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችሉ ጠንካራ ስራዎች መሰራታቸውም አብራርቷል።
በመጨረሻም የተገኙትን ውጤቶች የበለጠ በማጠናከር የጎደሉንን ደግሞ ስር ነቀል በሆነ ሁኔታ መፍታት የሚያስችል ጉባኤ ለማድረግ ሁሉም የጉባኤው ተሳታፊዎች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።