ኢተምድ ለ ኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን (ISO 9001) የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፍኬት ሰጥቷል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት የሚጠይቀውን የዓለም አቀፍ መመዘኛዎች በተከናወነውን የኦዲት ሂደት መስፈርቶችን በማሟላታቸው ሰርተፍኬቱ ተሰጣቷቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ ለኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም ሰርተፊኬቱን በሰጡበት ወቅት የእንኳን ደስአላችሁ መልእክትም አስተላልፈዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የኢፌድሪ የትርንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል ክቡር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡