ኢተምድ ለሦስት ድርጅቶች የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለንፋስ ስልክ ፖሊቴክኒክ ኮለጅ(ISO 21001) የትምህርት ተቋማት ስራ አመራር ሥርአት ፣ ለቤካስ ኬሚካልስ ኃ/የተ/የግ/ማ (ISO 9001) የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት እና ለፕሪማ ምግብ መቀነባበርያ ኃ/የተ/የግ/ማ (ISO 9001) የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላታቸውን በተከናወነላቸው የኦዲት ሂደት ተገምግሞ የተሰጣቸው ሲሆን ሰርቲፊኬቱን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ ለድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች አስረክበዋል፡፡