
ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ ዲኖች፣ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች የተገኙበት የልኡካን ቡድን በዘመናዊ የፍተሻ ቴክኖሎጂዎች የተደራጁትን የኢተምድ ላቦራቶሪዎች ጎበኙ፡፡ በጉብኝታቸው በሀገር ውስጥ የሚመረቱና ከውጪ የሚመጡ ምርቶችን ጥራት የሚያረጋግጡ በዘመናዊ የፍተሻ መሳሪያዎች የተደራጁ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዘጠኝ የፍተሻ ላቦራቶሪዎች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ ኢተምድ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና የሥራ እንቅስቃሴውን በተለይም ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በምርምርና አፕላይድ ሪሰርች ዘርፍ እና ተማሪዎችን በኢንተርሺፕ ተቀብሎ በተግባር ማብቃትና ማሰልጠን ላይ ኢተምድ ከትምህርት ተቋማቱ ጋር በጋራ እየሰራባቸው በሚገኝባቸው መስኮችና አገልግሎቶች ላይ ገለፃና ማብራሪያ አድርገውላቸዋል፡፡
Related Posts
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡