
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት እና የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎቶችን በዓለም አቀፍ የአሰራር ሥርዓት መሰረት ተግባራዊ ለማድረግ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ የስምምነቱን ሰነድ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መአዛ አበራ እና የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንድሙ ደንቡ ፈርመዋል።
ስምምነቱ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎቶችን በዓለም-አቀፍ አሰራር ሥርዓት መሰረት ተግባራዊ ለማድረግ የተደረገ ሲሆን የሎጅስቲክስ አገልግሎት በሀገራዊ እና ዓለም-አቀፋዊ ደረጃዎች መስፈርት መሰረት ጥራቱን በማረጋገጥ፣ተቋማዊ ልምድን ፣ሙያዊና ቁሳዊ ሀብትን አስተባብሮ በጋራ በመስራት የአገልግሎት ጥራት በማረጋገጥ የጥራት ጉድለት ሊያስከትል የሚችለውን ዘርፈ-ብዙ አሉታዊ ጉዳት በማስቀረት የኢንዱስትሪው ውጤታማነት፣ ቅልጥፍና እና ተወዳዳሪነት ላይ የሚኖረው ፋይዳ ትልቅ እንደሆነ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።