ኢተምድ ለኤዲዩ ኮሙኒኬሽን ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማ የተቀናጀ የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለኤዲዩ ኮሙኒኬሽን ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማ የተቀናጀ የሥራ አመራር ሥርዓት (በጥራት ሥራ አመራር ሥርአት፣በአካባቢ ሥራ አመራር ሥርዓት እና በሥራ ቦታ ጤናና ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት) ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡ ድርጅቱ የተቀናጀ የሥራ አመራር ሥርዓት ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላቱን በተከናወነለት የኦዲት ሂደት ተገምግሞ የተሰጠው ሲሆን ሰርቲፊኬቱን የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ ለድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አስረክበዋል፡፡ ኤዲዩ ኮሙኒኬሽን ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማ በቴሌኮም እና በአይሲቲ መሰረተ ልማት ሥራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው፡፡