የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ታዬ አጽቀ ስላሴ የጥራት መንደርን ጎበኙ።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ታዬ አጽቀ ስላሴ በቅርቡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀውን እና በዘመናዊ የፍተሻ ቴክኖሎጂዎችና ባለሙያዎች የተደራጀውን የጥራት መንደር ጎበኙ፡፡ ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው በዘመናዊ የፍተሻ መሳሪያዎች እና ባለሙያዎች የተደራጀውንና ደረጃቸውን የጠበቁትን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዘጠኝ የፍተሻ ላብራቶሪዎች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ እንዲሁም የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ኢተምድ እየሰጣቸው ስለሚገኘው አገልግሎቶች ገለፃና ማብራሪያ አድርገውላቸዋል፡፡