የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አመራሮችና ሠራተኞች የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለ13ኛ ጊዜ “ጥራት፡ መስፈርቶችን ከማሟላት ወደ ላቀ የአፈፃፀም ብቃት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን የዓለም የጥራት ቀንን በማስመልከት በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተዘጋጀውን የምርት ጥራት እና የሥራ አመራር ሥርዓት ማረጋገጫ ያገኙ ድርጅቶች ብቻ እየተሳተፉበት የሚገኘውን ኤግዚቢሽን በጥራት መንደር በመገኘት ጎብኝተዋል። ከኢግዚቢሽኑ በተጨማሪ ኢተምድ የጥራት ፍተሻ አገልግሎት የሚሰጥባቸው 9 ላብራቶሪዎች በመዘዋወር ጎብኝተዋል።


Related Posts
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡