ሀገራችን ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀዳሚ የጥራት ማዕከል የሚያደርጋትና የምርት ጥራትን ለማረጋገጥና ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችላት የተለያዩ የጥራት መሠረተ ልማቶችን በአንድ ቦታ ላይ አካቶ የያዘ የጥራት መንደር በዘመናዊ የፍተሻ ቴክኖሎጂዎች ተደራጅቶ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ተመርቋል፡፡ በዛሬው እለት ከተለያዩ መ/ቤቶች የተውጣጡ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አምራች ድርጅቶች እና የተለያዩ ማህበራት በጥራት መንደሩ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ከውጪ ሀገራት የሚገቡ እና በሀገራችን የሚመረቱ የተለያዩ ምርቶች የጥራት ደረጃ የሚፈተሽባቸውን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ላብራቶሪዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡ ፡በድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተቋሙ የምርትና አገልግሎቶችን ጥራት ከማስጠበቅ አንፃር እየሰጣቸው የሚገኘውን አገልግሎቶች በተመለከተ ገለፃም ተደርጎላቸዋል፡፡


Related Posts
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡