
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሠራተኞች በዘመናዊ የፍተሻ ቴክኖሎጂዎች ተደራጅቶ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የተመረቀውን የጥራት መንደር ጎብኝተዋል፡፡ የጥራት መንደሩ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅትን፣የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩትን የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩትን፣ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎትን እና የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣንን ያካተተ ነው፡፡
በጉብኝታቸውም የተቀናጀና ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ፍተሻ አገልግሎት ለመስጠት በዘመናዊ የፍተሻ መሳሪያዎች የተደራጁትን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዘጠኝ ላብራቶሪዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተቋሙ የምርትና አገልግሎቶችን ጥራት ከማስጠበቅ አንፃር እየሰጣቸው የሚገኘውን አገልግሎቶች በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።