በአፍሪካ ደረጃ በአይነቱና በሚሰጠው አገልግሎት ልዩ የሆነና የተቀናጀና ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ፍተሻ አገልግሎት ለመስጠት በዘመናዊ የፍተሻ መሳሪያዎች የተደራጁ 5 የተለያዩ የጥራት መሠረተ ልማቶችን አንድ አካቶ የያዘው ብሔራዊ የጥራት መንደር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋ ተመርቋል። የጥራት መንደሩ በውስጡ እጅግ ዘመናዊ መገልገያዎችን ያሟላ እጅግ የዘመኑ የፍተሻ ላብራቶሪዎች ያሉት የምርትና አገልግሎት ጥራት ማረጋገጫ ልቀት ማዕከል ነው። በጥራት መንደሩ ቅጥር ግቢ ለዉጪ ተገልጋዮች እና ለውስጥ ሠራተኞች በቂ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች፣ ለአይን የሚያምር የአገልግሎት ተጠቃሚዎችንና የውስጥ ሠራተኞችን መንፈስ የሚያድስ አረንጓዴ ስፍራም አካቶ የያዘ ነው።
በይፋ የተመረቀው ብሔራዊ የጥራት መንደርም በእሳቸው ሃሳብ አመንጪነትና ጥብቅ ክትትል እንዲሁም በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጠንካራ አመራር እና በጥራት መንደሩ አመራሮችና ሠራተኞች የጋራ ጥረት ሥራው ተጠናቆ ተመርቋል።
Related Posts
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ታዬ አጽቀ ስላሴ የጥራት መንደርን ጎበኙ።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አመራሮችና ሠራተኞች የጥራት ኤግዚቢሽንንና የኢተምድን ላብራቶሪዎች ጎበኙ
የዓለም የጥራት ቀን ለ13ኛ ጊዜ ተከበረ።