
ኢተምድ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 6,823 የአገልግሎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡
መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
====================
ኢተምድ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 6,823 አገልግሎቶችን በላብራቶር ፍተሻ፣በውጪና አገር ውስጥ ምርት ኢንስፔክሽን፣ በሠርተፊኬሽን እንዲሁም በጁቡቲ ወደብ በኩል ለ445,651.65 ሜ/ቶን የአፈር ማዳበሪያ እና ለ7,193,952.00 የምግብ ዘይት ኢንስፔክሽን አገልግሎት ሰጥቷል፡፡
ኢተምድ ዋና መ/ቤቱን አዲስ አበባ በማድረግ በ9 የተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ቅርንጫፍ በመክፈት እንዲሁም በውጭ ሀገር በጅቡቲ ወደብና በኬንያ ላሙ ወደብ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶችን በመስጠት ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገቶች አስተማማኝ መሠረት እንዲኖራቸው እና ቀጣይነታቸውን በማረጋገጥ አገራዊ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት በሚደረገው ርብርብ ሀላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።