ኢተምድ ለጉባ ላፍቶ አማካሪ አርክቴክቶችና መሐንዲሶች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።

ኢተምድ ለጉባ ላፍቶ አማካሪ አርክቴክቶችና መሐንዲሶች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።

መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ(ኢተምድ)

====================

ጉባ ላፍቶ አማካሪ አርክቴክቶችና መሐንዲሶች Quality Management System ISO 9001:2015 ተፈላጊ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት መስፈርቶችን በማሟላቱ ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በዛሬው እለት ስርተፊኬት አግኝቷል። ሰርተፍኬቱን በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ኃይለማርያም እና የጉባ ላፍቶ አማካሪ አርክቴክቶችና መሐንዲሶች ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ሽመልስ ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሰርቲፊኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ እንየዉ እጅ ተቀብለዋል፡፡

ለድርጅቱ ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ሌሎች በዘርፉ ስር ያሉ ድርጅቶቻችን መስፈርቶቹን በማሟላት በዘርፉ የተሻለ ዉጤት ለማምጣት እንደሚሰሩ አቶ ካሳሁን ኃይለማርያም ተናግረዋል። አክለውም የድርጅቱ ሰራተኞች የተገኘዉን የQuality Management System ISO 9001:2015 በተሻለ ሁኔታ ለማስቀጠል በርትተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አቶ አምሳሉ እንየው በበኩላቸው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ደርጅቶች የተለያዩ የተስማሚነት ምዘና መስፈርቶችን በማሟላት ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተናግረው። በተጨማሪም የድርጅቱ አመራር እና ሰራተኞች በኦዲት እና ሰርቲፊኬሽን ጊዜ ላደረጉት አስተዋጽኦ በማመስገን የተቀሩት የሚድሮክ ድርጅቶችም መስፈርቶቹን በማሟላት ለበለጠ ውጤት እንደሚሰሩ እምነታቸውን ገልጸዋል።