ኢተምድ ለብሉናይል ፕሮፕሊንና ክራፍት ከረጢት ማምረቻ የIntegrated Management System ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡

ኢተምድ ለብሉናይል ፕሮፕሊንና ክራፍት ከረጢት ማምረቻ የIntegrated Management System ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡

ነሃሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ(ኢተምድ)

======================

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አካል የሆነው ብሉናይል ፕሮፕሊንና ክራፍት ከረጢት ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማ Integrated Management System መስፈርት በማሟላት ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ሰርተፍኬት ተቀብሏል።

ሰርቲፍኬቱን አቶ ፀጋ ክፍሌ የብሉናይል ፕሮፕሊንና ክራፍት ከረጢት ማምረቻ ዋና ስራ አስኪያጅ የኢተምድ የጥራት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከሆነው አቶ ሙሉጌታ መሀሪ እጅ ተቀብለዋል፡፡ አቶ ፀጋ ክፍሌ ሰርተፍኬቱን በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ ድርጅታችን ሁሌም ለጥራት ቅድሚያ በመስጠት የሚሰራ ተቋም ነው ይህንን ልምዳችንንም በተጠናከረ ሁኔታ እንቀጥላለን በማለት ተናግረዋል።

አቶ ሙሉጌታ በበኩላቸው የብቃት ማረጋጋጫ ለማግኘት ብዙ መስፈርቶችን ማሟላት የሚጠይቅ ሲሆን ብሉናይል ፕሮፕሊንና ክራፍት ከረጢት ማምረቻ ይህን በማሳካቱ ለተጠቃሚዎች ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ በመሆኑ ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል። ድርጅቱ በዛሬው ዕለት የተቀበለው የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001፡2015)፣የአካባቢ ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO14001፡2015) እና የሥራ ቦታ ጤናና ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO45001:2018) ሰርተፍኬቶችን በማጣመር የሚሰጥ Integrated Management System ሰርተፍኬት ነው።