ኢተምድ ለሆራይዘን ፕላንቴሽንስ የቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የምግብ ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO22000:2018) ሰርተፍኬት ሰጠ።

ኢተምድ ለሆራይዘን ፕላንቴሽንስ የቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የምግብ ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO22000:2018) ሰርተፍኬት ሰጠ።

September 10,2024

አዲስ አበባ(ኢተምድ)

================

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ግብርና ዘርፍ አካል የሆነው ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ የቡና ማዘጋጃና ማከማቻ ኃ/የተ/የግ/ማ ISO 22000:2018 Food Safety Managements System መስፈርትን በማሟላት ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ሰርቲፊኬት ተቀብሏል።

ሰርቲፍኬቱን የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ነፃነት ጋሻዬና በሚድሮክ ኢንቨሰትመንት ግሩፕ የግብርና ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እንየው እጅ ተቀብለዋል፡፡ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የግብርና ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፈለቀ ታደሰ ሰርተፍኬቱን በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደሰታ በመግለፅ የድርጅታችን ሰራተኞች የተገኘውን ዉጤት ለማስቀጠል ተባብረን መስራት አለብን ብለዋል። ድርጅታችን በሁሉም ዘርፍ ለጥራት ቅድሚያ በመስጠት የሚሰራ ነው ይህንን ልምዳችንንም በተጠናከረ ሁኔታ እንቀጥላለን ብለዋል።

አቶ አምሳሉ እንየው በበኩላቸው በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኙ በርካታ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬቶችን እያገኙ መሆናቸውን በመግለፅ በተለይም የበላይ አመራሩን ቁርጠኝነት አድንቀዋል። የብቃት ማረጋጋጫ ለማግኘት ብዙ መስፈርቶችን ማሟላት የሚጠይቅ ሲሆን የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ የቡና ማዘጋጃና ማከማቻ ይህን በማሳካቱ ለተጠቃሚዎች ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ በመሆኑ ምስጋናችን የላቀ ነውም ብለዋል።