
የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአ እምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት የማአድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል፡፡
ጳጉሜ 4 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
========================
የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ጳጉሜ 4 የኅብር ቀንን ምክንያት በማድረግ በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአ እምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት የማአድ ማጋራት የምሳ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡
በፕሮግራሙ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ እንደ ሀገር የመስጠት ልምምድ ሊኖረን እንደሚገባ በመግለጽ በመስጠት የሚጎድል ነገር የለም ብለዋል፡፡ የመረዳዳት ባህልን ማዳበር እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የማነጅመንት አባላትም ጳጉሜ 4 የኅብር ቀን “ህብራችን ለሰላማችን” “አብረን ነበርን አብረን እንኖራለን” በሚሉ መሪ ሀሳቦች እለቱን ከሚኒስቴር መ/ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት በጋራ በመሆን በመቄዶንያየአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘትከ 7,500 በላይ ተረጂዎች ማዕድ የማጋራት እና ልዩ ልዩ ድጋፎችን በማድረግ እለቱን አክብረዋል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።