
በምርትና አገልግሎት ጥራት ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሄደ ፡፡
ነሃሴ 22 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
=======================
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተዘጋጀውና አራተኛ ቀኑን የያዘው “የኢትዮጵያን ይግዙ” የንግድ ሳምንት ኤግዚቪሽንና ባዛር አካል የሆነው በምርትና አገልግሎት ጥራት ዙሪያ የፓናል ውይይት ተከናውኗል፡፡ በመክፈቻ ፕሮግራሙ የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደ/ር ካሳሁን ጎፌ ባስተላለፉት መልእክት ያለ ምርት ጥራት የገበያ ውድድር እንደማይታሰብ፤ ጥራት የሁሉም ቋጠሮ መፍቻና የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ንግድ በማስተሳሰር አይተኬ ሚና ያለው መሆኑን እንዲሁም የኢትዮጵያን ይግዙ ስንል ከወጪ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ብሎም በጥራት እየተመረተ ያለውን የሀገራችንን ምርት ለመላው ዓለም ማስተዋወቅ እንደሚያስፈልግ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል::
የምርት ጥራትን ለማስጠበቅና ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን ሀገራችንን ከአፍሪካ ቀዳሚ የጥራት ማዕከል የሚያደርጋት የጥራት መሰረተ ልማት ተገንብቷል፡፡
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለሌሎች ሀገራት ምርት እያቀረበች ሲሆን የኢትዮጵያን ምርት መግዛት መልመድና ባህል ማድረግ ያስፈልጋል::
ኢትዮጵያ ያላትን የወጭ ንግድ ዕምቅ አቅም የሚያስተዋውቅ ቋሚ ኤግዚቪሽን ማዕከል ተገንብቶ መመረቁና ለጎብኝዎች ክፍት ተደርጎ እየተጎበኘም ይገኛል፡፡
በዚህ መድረክ በጥራት ዙርያ ሰፊ ልምድና እውቀት ያላቸው ተማራማሪዎች እና ባለሙያዎች ለውይይት የሚሆን የመነሻ ሃሳብ በማቅረብ ሰፊ ውይይት በማድረግ የጥራት ጉዳይ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ግንዛቤ ተወስዷል፡፡
Related Posts
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡