
የሠራተኞች የእውቅና አሰጣጥ መርሃ-ግብር ተከናወነ
ነሃሴ 20 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
============================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በ2016 በጀት ዓመት ላስመዘገበው የላቀ ስኬት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ፈፃሚ አመራርና ሠራተኞቹ በንግድና ቀጠናዊ ትስስርና ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ፣ ክቡር አቶ እንዳለው መኮንን በንግድና ቀጠናዊ ትስስርና ሚኒስቴር የጥራት ማረጋገጫ ዘርፍ ሚ/ር ዲኤታ እና ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስርና የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚ/ር ዲኤታ በተገኙበት እንደ አስተዋፅኦ ደረጃቸው የምስጋና የምስክር ወረቀት እና የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ይህ የእውቅና መርሃ ግብር በንግድና ቀጠናዊ ትስስርና ሚኒስቴር ሀሳብ አመንጪነት ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኘው አገር አቀፍ የንግድ ሳምንት አካል ሲሆን በእውቅና አሰጣጥ መርሃ- ግብሩ ላይ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ሀገር የምትሻገረው ጎበዞቿን ማክበርና ማበረታታት ስትችል እንደሆነ በመግለፅ እንዲሁም የሀገር ብልፅግና ሊረጋገጥ የሚችለው በታታሪ ልጆቿ እጆች በመሆኑ ይህ ዛሬ የተሰጣችሁ እውቅና እና ሽልማት ለበለጠ ውጤት ሊያተጋችሁ ይገባል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።