“የኢትዮጵያን ይግዙ” ልዩ የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር ተከፈተ፡፡

“የኢትዮጵያን ይግዙ” ልዩ የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር ተከፈተ፡፡

ነሃሴ 20 ቀን 2016ዓ.ም

አዲስ አበባ (ኢተምድ)

=======================

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው አገር አቀፍ የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽን በሚኒስቴሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ በይፋ ተከፍቷል፡፡

ኤግዚቢሽኑ ለሚቀጥሉት 5 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ገዥና ሻጭን ማገናኘት፣በዘርፉ ያለውን አቅም ማሳየት እንዲሁም ንግድን በተመለከተ ግንዛቤ የሚያሳድጉ ወርክሾፖች የሚደረጉበት መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ኢግዚቪሽንና ባዛሩን መርቀው የከፈቱት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር ናቸው፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያስገነባውን የወጪ ንግድ ምርቶች ማሳያ ማዕከልም በእለቱ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡

በዚህ ልዩ የንግድ ሳምንት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርቶችና አገልግሎቶችን ጥራት ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ የአሰራር ስርዓቶች መሰረት እየሰጣቸው የሚገኙ የፍተሻ ላቦራቶር፣የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎቶችን በተመለከተ ለኤግዚቢሽኑ ጎብኚዎች ገለፃ በማድረግ የድርጅቱን አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ ነው፡፡