የኢተምድ ሥራ አመራርና ሠራተኞች በእንጦጦ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አከናወኑ፡፡

የኢተምድ ሥራ አመራርና ሠራተኞች በእንጦጦ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አከናወኑ፡፡
ነሃሴ 17 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
========================
“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች እየተከናወነ ይገኛል። የዚህ ዘመን ተሻጋሪ አሻራን የመትከል መርሃ ግብር አካል በመሆን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) የሥራ አመራር አባላት እና ሠራተኞች ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው እለት በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ፓርክ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት ክቡር ዶ/ር ካሣሁን ጎፌ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር “የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ በሚተከልበት የዚህ ታሪካዊ ቀን አካል በመሆናችን እድለኞች ነን በማለት በችግኝ ተከላው ለተሳተፉ አመራሮችና ሠራተኞችም ምስጋና አቅርበው ለመላው የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳትፎ የተተከሉ ችግኞችንም በመንከባከብ እንዲደገም አሳስበዋል፡፡