ኢተምድ ለአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡

ኢተምድ ለአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡

ነሃሴ 09 ቀን 2016ዓ.ም

አዲስ አበባ (ኢተምድ)

====================

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡

በሰርተፊኬት አስጣጥ ስነ-ስርአቱ ላይ በመገኘት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አበራ ብሩ እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቁ እና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ማፍራት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን በማስታወስ ለዚህም ኮሌጁ የጥራት ሥራ አመራር ስርአት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ባለቤት መሆኑ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ይጨምራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ ሰርተፍኬቱን ባስረከቡበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በምዘና ስርአት ለማለፍ የአመራር ቁርጠኝነት እና የስራ ትጋት የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን በመግለፅ ለዚህም ኮሌጁ ያገኘው ሰርተፍኬት የአሰራር ስርአትን በማዘመን የደንበኞች እርካታን ለማሳደግ እንደሚረዳ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ግሩም ግርማ በበኩላቸው ኮሌጁ የደንበኞችን እርካታ መነሻ በማድረግ የ9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ስርዓትን ለመተግበር ከታህሳስ 2015 ጀምሮ ወደ ተግባር በመግባት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቶ የኮሌጁን ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ብሎም ለከተማ አስተዳደሩ እሴት የሚጨምር እውቅና ማግኘቱን ገልፀዋል። ከሰርተፊኬት አስጣጥ ስነ-ስርአቱ በኃላ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሂዷል፡፡