ኢተምድ ለኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡
ሐምሌ 30 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
======================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በስልጠና፣ በጥናትና ምርምር፣በቴክኖሎጂ እና በኢንተርፕራይዝ ልማት እና በዋና ካምፓሱ የሚገኙ ደጋፊ የሥራ ሂደቶች ባካተቱ ወሰኖች የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡
የጥራት የምስክር ወረቀቱን ከኢትዮጵያ የተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የሰርቲፊኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ እንየው እጅ የወሰዱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ ሰርተፊኬቱን ለማግኘት ያለፈባቸውን በርካታ ሂደቶች በመግለፅ ዋናው ነገር የምስክር ወረቀቱን ማግኘት ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ስራዎችን በስታንዳርዱ መሰረት በበለጠ ጠንክሮ መስራት ነው ብለዋል።
በስነስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ ለዚህ በመብቃቱ የበላይ አመራሩና ሰራተኞች ላሳዩት ቁርጠኝነት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ሥርዓቱ የሥራ ባህልን የሚቀይርና ከዓለምአቀፍ መሰል ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት ወሳኝ ሚናን እንደሚኖረው ገልጸዋል። ለዚህም ሲባል ወደዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ የሚቀላቀሉ ዜጎች የሚጠበቅባቸውን ደረጃ ማሟላት ሰላሉባቸው የስልጠና ተቋማትም የዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን እንዲያሟሉ ይደረጋል ብለዋል።
የኢተምድ የሰርቲፊኬሽን ዳይሬክትሬት ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ እንየው ሰርተፍኬት የመስጠት መርሃ ግብሩ ላይ በጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ዓለም አቀፍ የአሠራር ሥርዓትን ለመተግበር ኢንስቲትዩቱ ላሳየው ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ለሥራ አመራር አባላቱ እና ለሠራተኞቹ ያላቸውን አድናቆት በመግለፅ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
Related Posts
ኢተምድ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 6,823 የአገልግሎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡
ኢተምድ ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።
ኢተምድ ለራህመት መሃመድ ዱቄት ፋብሪካ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።