
የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት በተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ሽኝት ተደረገላቸው፡፡
ሐምሌ 17 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
====================
የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት መሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ እንዳለው መኮንን እና የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) የኢትዮጵያ ተወካይ እና በአፍሪካ ህብረት የቀጠናው ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉትን ኦሬሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡
በሚኒስቴር መ/ቤቱ የጥራት መሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ኦሬሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ በነበራቸው የስራ ጊዜ በጥራት መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በተለይም በማር እሴት ሰንሰለት የጥራት ቁጥጥር አቅም ግንባታ ፕሮጀክትን በመደገፍ ላበረከቱት አመራርነት አመስግነው፤በራሳቸውና በጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ስም ቀጣይ የሥራ ዘመናቸው የተቃና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።