የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን ከተጠሪ ተቋማት ጋር እየገመገመ ነው፡፡

የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን ከተጠሪ ተቋማት ጋር እየገመገመ ነው፡፡

ሐምሌ 03 ቀን 2016ዓ.ም

አዲስ አበባ (ኢተምድ)

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተጠሪ ተቋማትን የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም የዋና መ/ቤቱ እና የስድስቱ ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የግምገማ መድረክ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም በመገምገም ለ2017 በጀት ዓመት በቂ ዝግጅት ለማድረግ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን፣ ያልተከናወኑ ተግባራትን እና በአፈፃፀም ወቅት ያጋጠሙ እክሎችን ለመለየት አጭርና ውጤታማ ግምገማ በማካሄድ ተልዕኮውን መሸከም የሚችል ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እና ጠንካራ የሥራ አመራር አባላት ለመፍጠር የግምገማውን አስፈላጊነት ገልፀው መድረኩን አስጀምረዋል፡፡ የ2017 በጀት ዓመት ከሐምሌ 01 ጀምሮ የትግበራ ምእራፍ መሆኑን በመገንዘብ ለውጤታማነቱ መረባረብ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመድረኩ የስድስቱ ተጠሪ ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡