የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር በብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡
ሐምሌ 02 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት የቢሮና የላብራቶሪ ግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ በአካል በመገኘት ክትትልና ድጋፍ አደረጉ፡፡
ፕሮጀክቶቹ እንደሀገር ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸው መሆናቸውን አፅንኦት በመስጠት የፕሮጀክቶቹ ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ በመግለፅ ሁሉም በዚህ ፕሮጀክት ተሳታፊ የሆኑ አካላት ደግሞ ለፕሮጀክቶቹ በተለየ መልኩ ትኩረት ሰጥተው በፍጥነት እና በጥራት ተጠናቀው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ክትትልና ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
Related Posts
ኢተምድ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 6,823 የአገልግሎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡
ኢተምድ ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።
ኢተምድ ለራህመት መሃመድ ዱቄት ፋብሪካ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።