ኢተምድ ለሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ/የተ/የግ/ማ የ”ISO 14001:2015 Environmental Management system”ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡
ሰኔ 19 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
====================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር ለሚገኘው ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ/የተ/የግ/ማ በአካባቢ ጥበቃ ሥራ አመራር ሥርአት (ISO:14001፡2015 Environment Management Systems/EMS/ ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡
የኢተምድ የኮርፓሬት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጋሻው ተስፋዬ ሰርተፍኬት የመስጠት መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት በአካባቢ ጥበቃ ሥራ አመራር ሥርአት ዓለም አቀፍ የአሠራር ሥርዓትን ለመተግበር ግሩፑ ላሳየው ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ለድርጅቱ የሥራ አመራር አባላት እና ለሠራተኞቹ ያላቸውን አድናቆት በመግለፅ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማእድን ክላስተር ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዱላ መኮንን በአካባቢ ጥበቃ ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ለማግኘት ኢተምድ ላደረገላቸው ሙያዊ የኦዲት ስራዎችና ለተሰጣቸው ሰርተፍኬት አመስግነው፤በቀጣይም የአካባቢ ሥራ አመራር ሥርአትን ጨምሮ ሌሎች የሥራ አመራር ሥርዓቶችን በማጣመር በመተግበር ጥራትን ለማረጋገጥ የሶስተኛ ወገን የማረጋገጫ አገልግሎት ለድርጅቶች ቀጣይነት የሚኖረው አስተዋፅኦ መሰረታዊ በመሆኑ የተጀመረውን ሥራ በሌሎች ዘርፎችም ለማስቀጠል በጋራ መስራት የድርጅታቸው ፍላጎት መሆኑን ሰርተፍኬቱን ከኢተምድ የኮርፓሬት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጋሻው ተስፋዬ በተቀበሉበት ጊዜ ገልፀዋል፡፡
Related Posts
ኢተምድ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 6,823 የአገልግሎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡
ኢተምድ ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።
ኢተምድ ለራህመት መሃመድ ዱቄት ፋብሪካ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።