የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለሥራ መሪዎችና ሠራተኞቹ “ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርእስ እንዲሁም በሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ቀን ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
=========================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት “ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርእስ እንዲሁም በሌሎች በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለሰራተኞቹ ለሁለት ቀናት ሲሰጠ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ስልጠናው በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ የመክፈቻ ንግግር በማደረግ የተጀመረ ሲሆን ሰራተኞች በዚህ ስልጠና ከእዳ ወደ ምንዳ ለመሸጋገር የሚያስችሉ ወቅታዊ ሃገራዊ አጀንዳዎች ላይ በመወያየትና በመመካከር የተሻለ ግንዛቤ በመፍጠር ሰራተኛው የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ለማድረግ፣መንግስት የጀመረው የለውጥ ጉዞ የኢትዮጵያዊያንን ማህበራዊ መስተጋብርና ትሥሥር በአዲስ ሀገራዊ ገዥ ትርክት ለመገንባት ፈር የቀደደ የለውጥ ጉዞ መሆኑን፣ ሀገራዊ ኢኮኖሚያችንን ከፍፁም ቀውስና ከፍተኛ የዕዳ ጫና ለመታደግ የሚያስችል ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በመተግበር ተጨባጭ ለውጦችን ማየት የጀመርንበት ጊዜ ላይ በመድረሳችን ሪፎርሙን ውጤታማና ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ ለማድረስ ጠንካራ ተቋምና ዘመናዊ አሰራር የሚተገብሩ ሰራተኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን መላው ሰራተኛ ግንዛቤውን ያሳደገበት መድረክ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
የመጀመሪያው ቀን ስልጠና የድርጅቱ የኮርፖሬት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ጋሻው ተስፋዬ ሃብት የመፍጠር ጉዞአችን፣ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም በሁለተኛው ቀን ስልጠናም በአቶ አቤል አንበርብር የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የመንግስት ሰራተኛው ሚና በሚል ርእስ ለሰራተኞች ገለፃ አድርገዋል፡፡
ሰራተኞችም በስልጠናው ላይ ሰፊ ውይይትና የነቃ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ ስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይም የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ በስልጠናው ላይ በሰራተኞች የተነሱት ድርጅቱን የሚመለከቱ ዋና ዋና አንኮር ጉዳዮች የሚመለከታቸውን የስራ ክፍሎች የድርጊት መርሃ-ግብር (action Plan) ተዘጋጅቶ ለተፈፃሚነታቸው ሁሉም ሰራተኛ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በተጨማሪ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ስልጠናውን አጠቃለዋል።


Related Posts
የኢተምድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀንን አከበረ፡፡ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ)
“ጥራት፡ በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ቃል የዓለም የጥራት ሳምንት በጥራት መንደር ውስጥ የተዘጋጀውን የጥራት ኤክስፖ ተጠናቀቀ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በተገኙበት አምስት ተቋማትን በአንድ ላይ በመያዝ የተደራጀው የጥራት መንደር አንደኛ ዓመት በዛሬው ዕለት በደማቅ መረሃ ግብር ተከብሯል ።