የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለሥራ መሪዎችና ሠራተኞቹ “ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርእስ እና በሌሎች ዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለሥራ መሪዎችና ሠራተኞቹ “ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርእስ እና በሌሎች ዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ(ኢተምድ)

=========================

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት “ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርእስ እና በሌሎች በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለሰራተኞቹ ስልጠና መስጠት ጀመረ። ለሁለት ቀናት በሚሰጠው ስልጠና ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ የዚህ የስልጠና ዋነኛ ዓላማ ሁሉም የድርጅቱ ሰራተኞች ከእዳ ወደ ምንዳ ለመሸጋገር የሚያስችሉ ወቅታዊ ሃገራዊ አጀንዳዎች ላይ በመወያየትና በመመካከር የተሻለ ግንዛቤ በመፍጠር  ሰራተኛው የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ለማስቻል ነው። መንግስት የጀመረው የለውጥ ጉዞ የኢትዮጵያዊያንን ማህበራዊ መስተጋብርና ትሥሥር በአዲስ ሀገራዊ ገዥ ትርክት ለመገንባት ፈር የቀደደ የለውጥ ጉዞ መሆኑን፣ ሀገራዊ ኢኮኖሚያችንን ከፍፁም ቀውስና ከፍተኛ የዕዳ ጫና ለመታደግ የሚያስችል ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በመተግበር ተጨባጭ ለውጦችን ማየት የጀመርንበት ጊዜ ላይ በመድረሳችን ሪፎርሙን ውጤታማና ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ ለማድረስ ጠንካራ ተቋምና ዘመናዊ አሰራር የሚተገብሩ ሰራተኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ ፕሮግራሙን አስጀምረዋል።

የመጀመሪያው ቀን ስልጠና የድርጅቱ የኮርፖሬት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ጋሻው ተስፋዬ ሃብት የመፍጠር ጉዞአችን፣ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚል ርእስ በመካሄድ ላይ ይገኛል።