ኢተምድ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት “ወደ ዓለም አቀፍ የተመጣጠነ ምግብ ደኅንነት” /Towards Global Food and Nutrition Security›› በሚል መሪ ቃል ከጳጉሜ 1-2/2015 ዓ/ም የተዘጋጀውን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የእንሰት ሲምፖዚየም በሚሰጠው የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት አጋር በመሆን ሀገር በቀል ምርቶችን በጥናትና ምርምር በመታገዝ በምርምር የተገኙ ውጤቶች፣ ወደ ማኅበረሰቡ በማድረስ ለምግብ ዋስትና ወሳኝ የሆነው እንሰት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ ሰፊውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ እንዲያደርግ ዩኒቨርሲቲው እያደረገ ያለውን ሥራ በመደገፍ ተቋማዊ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በዚሁ ሲምፖዚየም ላይ በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን በመሳተፍ ኢተምድ የምርትና አገልግሎቶችን ጥራት ለማስጠበቅ እየሰጣቸው የሚገኘውን የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶች በተመለከተ በሲምፖዚየሙ ለተሳተፉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡
Related Posts
ኢተምድ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 6,823 የአገልግሎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡
ኢተምድ ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።
ኢተምድ ለራህመት መሃመድ ዱቄት ፋብሪካ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።