
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) የሥራ አመራር አባላት እና ሰራተኞች ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ከሌሎች ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ከሆኑ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ሐምሌ 25ቀን 2015ዓ.ም በሰበታ ሀዋስ ወረዳ ደበል ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል፡፡
በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ የድርጅቱ የበላይ አመራሮች እንደሀገር የተያዘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ችግኝ መትከል ለትውልድ የሚተላለፍ ቅርስ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ ተግባር እንደሆነ እና ለተተከለው ችግኝም ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ስራ መሆኑን መልእክት አስተላልፈዋል።
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።