
የኢ.ፌ.ዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የስራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የፍተሻ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ፡፡ የጉብኝቱ ዓላማ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርቶችንና አገልግሎቶች ጥራትን ከማስጠበቅ አንፃር ያለውን አገልግሎት የመስጠት አቅም በአካል ተገኝተው በመጎብኘት በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ነበር፡፡
በጉብኝቱም በግዥ ሂደት ውስጥ የሚካተቱ ምርቶች በተስማሚነት ምዘና ሂደት ውስጥ የሚያልፉበትና የጥራት ቁጥጥር የሚደረግበትን አግባብ በመዘርጋት የተሻለ ጥራት ያለው ምርት በመግዛትና በማቅረብ የግዥ አፈፃፀም ሥርዓቱን የበለጠ ሀብትና ጊዜ ቆጣቢ እንዲሁም በውድድር ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማስቻል በቅንጅት በመስራት አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን ለማስገኘት በሚያችሉ ሁኔታዎች ላይ ከኢተምድ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።