
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ክትትልና ድጋፍ ከሚያደርግባቸው የፌደራል መ/ቤቶች አንዱ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ሲሆን የኢተምድን ተግባራትና አሰራር፣የሚሰጣቸውን የጥራት ፍተሻ ላብራቶር፣የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎቶች እና ተደራሽነቱን ለማስፋት እያከናወናቸው በሚገኙ የአቅም ግንባታ ተግባራት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ሰኔ 17 ቀን 2015ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሰጥቷል፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫው በድርጅቱ ተግባራትና አሰራር ላይ ግልፅነት በመፍጠር የቋሚ ኮሚቴውን የክትትልና ድጋፍ ስራ ውጤታማ ለማድረግ ያለመ ነበር፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።