
አነስተኛ እና መካከለኛ ምግብ አምራች ድርጅቶች የምግብ ደህንነት እና የጥራት ደረጃን ለማሻሻል የሚያስችል ስምምነት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በFood Enterprise Solutions መካከል ተደረገ፡፡
ስምምነቱ በአነስተኛ እና መካከለኛ የምግብ አምራች ኩባንያዎች የሚሰሩ ስራዎችን በቅንጅት የማስተባበርና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ምርቶቻቸውን እንዲያሻሽሉ፣የምግብ አያያዝና አቅርቦትን እንዲሁም የዘርፉን ንግድ ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።
ሀገር አቀፍና ዓለምአቀፍ የምግብ ደህንነትና የጥራት ደረጃ አስተዳደርን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መደገፍ እንዲሁም የምግብ ደህንነትና የጥራት ደረጃቸውን ላሻሻሉ እና መስፈርቱን ላሟሉ አነስተኛ እና መካከለኛ አምራቾች የጥራት ሰርተፍኬት መስጠት የሚሉትን ያካተተ ስምምነት ነው፡፡
ይህንን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት በመስጠት ረገድ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑን በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት ተገልፆል፡፡ በተጨማሪም የFood Enterprise Solutions ፕሬዘዳንት የሆኑት Mr Russ Webster ኢተምድ የምግብ ደህንነትና ጥራትን የሚፈትሽባቸውን የባዮ ኬሚካልና ሌሎች ላቦራቶሪዎችን አቅም ጎብኝተዋል፡፡
Related Posts
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡