የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች ክብርት ሁሪያ አሊ፣ክቡር ዶ/ር ባይሳ በዳዳ፣ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ተመራማሪዎች በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት/ኢተምድ/ በመገኘት የሥራ ጉብኝት አደረጉ።
በጉብኝቱ በኢተምድ የሚገኙትን የፍተሻ ላብራቶሪዎች፣የሚሠጡት የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች እና የአቅም ግንባታ ሥራዎች በአካል በመገኘት የጎበኙ ሲሆን በቀጣይ ኢተምድ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማዘመን እና በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በጋራ ተቀናጅቶ ለመስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

Related Posts
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡