በገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት/ኢተምድ/ በመገኘት የሥራ ጉብኝት አደረጉ።
የጉብኝቱ አላማም በድርጅቱ የሚሠጡት የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች እና በዓለም ባንክ ፕሮጀክት እየተሰሩ ያሉትን የአቅም ግንባታ ሥራዎች በአካል በመገኘት ያሉበትን ደረጃ መጎብኘት እና በቀጣይ ድርጅቱ የሚሰጠውን አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ እንዲያከናውን ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ ተቋም እንዲሆን ያለመ ነበር፡፡

Related Posts
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡