
127ኛው የዓድዋ ድል በዓልን “የዓድዋ ድል በዓል ለአገራዊ አንድነት፣ጀግንነት እና ጽናት መህልቅ” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት እና የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት የሥራ አመራር አባላት እና ሰራተኞች በጋራ አከበሩ፡፡
በዓሉን የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የከፈቱት የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሠረት በቀለ ዓድዋ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን በመሆኑ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊኮራበት የሚገባ መሆኑና ዓድዋ ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያዊያን የጋራ መስዋዕትነት ተከፍለውበት የተገኘ ድል በመሆኑ ከሀገር ኩራትነት ባሻገር በዓለም ለሚገኙ ጥቁር ህዝቦች በሙሉ የኩራት ምልክት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በበዓሉ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ቀኑን በማስመልከት ያዘጋጀው አጭር የመወያያ ፅሁፍ ቀርቦ ከተሳታፊ ሰራተኞች አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መአዛ አበራ በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ከዓድዋ ድል የወሰድነውን የጀግንነት መንፈስ በወቅታዊው ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ልንጠቀምበት እንደሚገባ ገልፀው የአሁኑ ትውልድ ሀገራችን ካለችበት የድህነት ታሪክ የማሻገር ድርሻውን ለመወጣት በዓድዋ ጀግኖቻችን የትብብርና የአንድነት መንፈስ ሁሉም የዜግነት ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡


Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።