
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በዓለም አቀፍ የአሰራር ስርዓቶች ተጨማሪ እውቅና አገኘ።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) በፍተሻ ላቦራቶር ISO/IEC 17025 ፣በኢንስፔክሽን ISO/IEC 17020፣ በሥራ አመራር ስርዓት ISO/IEC 17021 እና በምርት ሰርቲፊኬሽን ISO/IEC 17065 መሰረት ዓለም አቀፍ እውቅና እና ተቀባይነት ያለው የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ኢተምድ ዓለም አቀፍ እውቅናውን በማስፋት ተጨማሪ በምርት ሰርቲፊኬሽን ISO/IEC 17065 በዘጠኝ የምርት አይነቶች፣በኢንስፔክሽን ISO/IEC 17020 አስር የኢንስፔክሽን አይነቶችን በማስጠበቅና አዲስ በመጨመር እንዲሁም በጥራት ሥራ አመራር ስርዓት ዓለም አቀፍ እውቅናውን በኢትዮጵያ የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ማረጋገጥ ችሏል፡፡
Related Posts
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡