
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ከዓለም አቀፍ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር ያስገነባው የፀሐይ ኃይል ምርቶች መፈተሻ ላቦራቶሪ ሥራ ጀመረ። ላቦራቶሪው እስከ 350 ዋት የሚደርሱ የፀሐይ ኃይል ምርቶችን ለመፈተሽ የሚያስችል አቅም አለው።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ በላብራቶሪው ምርቃት ስነ-ስርዓት ወቅት እንደገለጹት ከውጭ የሚገቡና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ ምርቶችን ጥራት ለማረጋገጥ በኢተምድ በርካታ ሥራዎች ሲሠሩ ቆይተዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ ዘመናዊ በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ ምርቶች መፈተሻ ላቦራቶሪ ተገንብቶ ወደ ሥራ መግባቱን ጠቁመዋል። ላብራቶሪው ለገጠር ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚውሉ የፀሐይ ኃይል ምርቶችን በመፈተሽና የምስክር ወረቀት በመስጠት እንዲሁም ከተቆጣጣሪ መ/ቤቶች ጋር በመስራት ጥራት የሌላቸውን ምርቶች ከገበያ ውጭ በማድረግ የተጠቃሚውን ህብረተሰብ ደህንነት ለመጠበቅ እንደሚያስችልም ገልጸዋል፡፡ ከውጪ የሚገቡ ምርቶች ኢትዮጵያ ያወጣቺውን አስገዳጅ መስፈርቶች ማሟላታቸውን የቅድመ ጭነት ፍተሻ በማድረግ በሚያገኙት ማረጋገጫ ምርቶቹ እንደሚገቡም ተገልጿል፡፡
Related Posts
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡