ኢተምድ ከFITI Testing & Research Institute ጋር በመተባበር ለቆዳና ጨርቃጨርቅ ፍተሻ ባለሙያዎች ስልጠና እየሠጠ ይገኛል፡፡
ከኮሪያው የፍተሻ ላቦራቶርና የምርምር ኢንስቲትዩት (FITI Testing & Research Institute) ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የቆዳና ጨርቃ ጨርቅ ፍተሻ ባለሙያዎች በ5 የተለያዩ የፍተሻ ባህሪያት ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
የአቅም ግንባታ ስልጠናው በቆዳና ጨርቃ ጨርቅ ፍተሻ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተቀባይነትና እውቅናን በጠበቀ መልኩ ድርጅቱ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን በስራ ላይ ስልጠና፣ የልምድ ልውውጥ፣ ቴክኒካል ሙያዊ ድጋፍ፣ የፍተሻ ዘዴዎችን ማበልፀግ፣ በሌሎች ሀገራት በሚደረጉ የፍተሻ ንፅፅር ላይ ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንዲሁም በቆዳና ጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ የሰርቲፊኬሽን ወሰኖችን ለማስፋት የሚያስችሉ ቴክኒካል ድጋፎ ችን ያጠቃልላል፡፡




Related Posts
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢተምድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡
የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሥራ እንቅስቃሴ ገመገሙ፡፡
ኢተምድ በአዳማ ከተማ ያስገነባውን ህንፃ እና የፍተሻ ላብራቶሪ በይፋ አስመረቀ። ጥር 16/2018 ዓ/ም አዳማ (ኢተምድ)