የዓለም የጥራት ቀን ኤግዚቢሽን ተከፈተ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ጋር በጋራ የዓለም የጥራት ቀንን አስመልክቶ ያዘጋጁት ኤግዚቢሽን ተከፈተ። ኤግዚቢሽኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ ከሌሎች የዘርፉ ሚ/ዲኤታዎች እና የተቋማቱ ዋና ዳይሬክተሮች ጋር በጋራ ከፍተውታል። “በጥራት የተቃኘ ህሊና ትክክለኛ ተግባርን ለመከወን” በሚል መሪ ቃል የተከፈተው ይህ ኤግዚቢሽን ከህዳር 15-17/2015ዓ.ም ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከአራቱም የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ጋር በጥራት ዙሪያ የሚሰሩ የምርት ጥራት ማረጋገጫ ያገኙ ድርጅቶች ተሳትፈውበታል፡፡ ኤግዚቢሽኑ ለሶስት ቀናት ለህዝብ ክፍት የሚሆን ሲሆን ህብረተሰቡ  በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ በመገኘት ይህንን ኤግዚቢሽን እንዲጎበኝ ተጋብዟል፡፡