
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማ በምግብ ደህንነት ስራ አመራር ስርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በምግብ ደህንነት ስራ አመራር ስርዓት ISO: 22000:2018 ደረጃ መስፈርትን በማሟላታቸው የምግብ ማሸጊያ የቆርቆሮ ጣሳ በማምረት (producing, packing and storing of tin can for food packaging) ለዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማ ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡ የዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማ ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ መአዛ መርሻ በምግብ ደህንነት ስራ አመራር ስርዓት ሰርተፊኬት ለማግኘት ኢተምድ ላደረገላቸው ሙያዊ የኦዲት ስራዎችና ለተሰጣቸው ሰርተፍኬት አመስግነው፤በቀጣይም ጥራትን ለማስጠበቅ በጋራ መስራት የድርጅታቸው ፍላጎት መሆኑን ሰርተፍኬቱን ከኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መአዛ አበራ በተቀበሉበት ጊዜ ገልፀዋል፡፡
Related Posts
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡