ኢተምድ የትውውቅ መርሐ-ግብር አከናወነ፡፡

ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለቀጠራቸው አዲስ ሰራተኞች የትውውቅ መርሐ-ግብር አከናውኗል፡፡ መርሐ-ግብሩ አዲሶቹን ሰራተኞችን ከድርጅቱ ጋር ለማዋሃድ  የኢተምድን የአሰራር ስርአቶች፣የድርጅቱን ባህል፣ እሴቶችን እና ድርጅቱን  በተመለከተ ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን  በመስጠት ግንዛቤ መፍጠርን አላማው ያደረገ ነው። እንዲሁም አዲስ ሰራተኞች ወደ አዲስ የስራ አካባቢ በሚቀላቀሉበት ጊዜ የሚፈጠር የእንግድነት ስሜትን ለማስቀረት እና ከነባር ሰራተኞች ጋር ለማስተዋወቅ ያለመ ነው፡፡

በትውውቅ መርሐ-ግብሩ ላይ የኢተምድን ገፅታ፣ የዋና የስራ ሂደቶች አሰራር፣ የሰው ሃብት መመሪያዎች እና የሰራተኛ መብትና ግዴታ በተመለከተ ገለፃ የቀረበላቸው ሲሆን አዲስ  ተቀጣሪ ሰራተኞችም ግልፅ እንዲሆንላቸው የሚፈልጉትን ጥያቄዎች በማንሳት ምላሽ ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ተሰጥቷቸዋል፡፡ በመርሐ-ግብሩ መጨረሻ የድርጅቱን የፍተሻ ላብቶሪዎችም ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን አዲስ ተቀጣሪ ሰራተኞችም ስለተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ በማመስገን የድርጅቱን ስራዎች ለማወቅ እንዳስቻላቸው እና በሌሎች ድርጅቶችም ቢለመድ ጥሩ ተሞክሮ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡