
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም
ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ኢተምድን ጎበኙ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በሆኑት በወ/ሮ አይሻ ያህያ የተመራው የቋሚ ኮሚቴ አባላት ጥር 23 ቀን 2014ዓ.ም በኢተምድ በመገኘት የመስከ የሥራ ጉብኝት በማካሄድ ወቅታዊ የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ከተሰጠው ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት አንዱ የአስፈፃሚ ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን መስራት ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞም ኮሚቴው በኢተምድ ስራዎች ዙሪያ ውይይትና የመስክ ጉብኝት አካሂዷል።
ኢተምድ የሸማቾችንና የአካባቢን ጤናና ደህንነት በመጠበቅ በፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ የንግድ ውድድር ለማስፈን እና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ እንዲገነባ እየሰራቸው ስለሚገኙ የላብራቶር ፍተሻ፣ኢንስፔክሽንና ሰርቲፊኬሽን ስራዎች እንቅስቃሴ በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ተሻለ በልሁ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ በዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ የተደረገላቸው የቋሚ ኮሚቴው አባላት የኢተምድን ዘጠኝ ላብራቶሮች ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን የሚከናወኑ የገቢና ወጪ ምርቶች የጥራት ፍተሻ ስራዎች ለማከናወን ከውጪ የሚገቡ ለስራው አስፈላጊ ግብዓቶች እጥረት እና የደረጃዎች ትግበራ አስገዳጅና አስገዳጅ ያልሆነ መባሉ የአገልግሎት ፈላጊው ቁጥር የተፈለገውን ያህል እንዳይሆን በማድረግ ችግር እንደፈጠረ መረዳታቸውን በመጥቀስ ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ አማራጮችን መመልከት ይገባል ብለዋል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው ከድርጅቱ ጋር በቀጣይ ግንኙነቶቹ እንደሚጠናከሩ የገለጹት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ አይሻ ያህያ ስለ ድርጅቱ በቂ ግንዛቤ ህብረተሰቡ ኖሮት የአገልግሎት ተጠቃሚ ቁጥር እንዲጨምር አስፈላጊው የማስተዋወቅ ስራዎች ከድርጅቱ እንደሚጠበቅ ጠቁመው ኢተምድ እያከናወናቸው ስላሉት ተግባራት በቂ መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።