የአዲሱ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር በሆኑት አቶ ገብረመስቀል ጫላ የተመራ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከኢተምድ እና ከሶስቱ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት የሥራ አመራር አባላት ጋር በመሆን የተቋማቶቹን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም የአራቱ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት የአሰራር ስርዓት እና አገልግሎት በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
የሥራ ኃላፊዎቹ የኢተምድን ላብራቶሮች ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ድርጅቱ ካለው እና እየገነባ ከሚገኘው አቅም አንፃር በርካታ ስራዎች እየሰራ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ገልፀው ለወደፊትም በርካታ ሥራዎች መስራት የሚጠበቅበት የሀገራቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሊሆን የሚገባው ተቋም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ክቡር አቶ ገ/መስቀል ጫላ በቀጣይ በዘርፉ ያሉ የስራ አፈፃፀሞችን ለማሻሻል የሚያስችል የ100 ቀናት እቅድ በማዘጋጀት ትኩረት ተደርጎ ሊሰሩ የሚገቡ ስራዎችን ለይቶ በማቀድ እንዲሰሩ የስራ መመሪያ በመስጠት ተቋማቶቹ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚፈልጉት ድጋፎች እንደማይለያቸው በማረጋገጥ የሥራ ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል፡፡
Related Posts
ኢተምድ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 6,823 የአገልግሎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡
ኢተምድ ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።
ኢተምድ ለራህመት መሃመድ ዱቄት ፋብሪካ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።