አረንጓዴ አሻራ
በኢትዮጵያ የደን ኃብት ስነ-ምሕዳር ከግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው፡፡ ብርቅዬ የአገሪቱ የዱር አራዊትና አዕዋፍት፣ እንሰሳት እንዲሁም ደኑ የአካባቢውን ስነ-ምሕዳር ሚዛን በመጠበቅ ረገድ የራሱን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል። ባለፉት ዓመታት የሀገሪቱ የደን ቦታዎች ለእርሻና መኖሪያነት ለመሳሰሉ አገልግሎቶች በመፈለጋቸው የደኑ ሽፋን በፈጣን ሁኔታ በመራቆት ላይ ይገኛል። የደን ሀብትን ማልማት የአየር ንብረትለውጥ እያደረሰ ያለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቋቋም ትልቅ ሚና የሚጫወት በመሆኑና በሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ በደን መመናመን ምክንያት እየተከሰተ ያለውን አካባቢያዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመግታት ዘላቂ የደን ልማትና ጥበቃ ወሳኝ ሚና አለው፡፡
የደን ሀብትን ማብዛት እየተከሰተያለውን የአፈር መሸርሸር፣የበረሃማነት መስፋፋትና የብዝሐ ሕይወት መመናመን በመግታት የግብርናውን ዘርፍ ልማት በማፋጠንና በማስቀጠል ምርታማነቱን ለመጨመርና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ድርሻ ያለው በመሆኑ፤መንግስት ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃያ ወጣቸውን ፖሊሲዎችና እና ስትራቴጂዎች ለማስፈጸም በየዓመቱ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አመራር እና ሰራተኞችም ይህንን አገራዊ አላማ በመደገፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀንን በማስመልከት “50ኛው ዓመት 50ሺ ችግኝ” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ የጥራት ቁጥጥር ስራ የተጀመረበትን 50ኛ ዓመት ለመዘከር በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ደበል ተራራ አካባቢ በሁለት ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አከናውነዋል፡፡
Related Posts
ኢተምድ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 6,823 የአገልግሎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡
ኢተምድ ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።
ኢተምድ ለራህመት መሃመድ ዱቄት ፋብሪካ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001:2015) ሰርተፊኬት ሰጠ።